ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ አስፈርሟል

በአሠልጣኝ አስራት አባተ የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ የአንድ አጥቂ ዝውውር አገባዷል።
\"\"
ከሰዓታት በፊት የነባር ተጫዋቻቸው ቻርለስ ሙሴጌን እና ሱራፌል ጌታቸውን ውል ያራዘሙት ድሬዳዋ ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት የአንድ አጥቂ ዝውውር ማገባደዳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ተመስገን ደረሰ ነው። የቀድሞው የወልቂጤ ከተማ፣ የጅማ አባጅፋር እና ባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የነበረው የመስመር እና የመሐል አጥቂው ተመስገን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአርባምንጭ ከተማ በማሳለፍ ዘጠኝ ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ቀጣይ ማረፊያው የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ሆኗል።