ፈረሰኞቹ ጋናዊ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ተሰምቷል

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት ዓመት ውል የጋና ዜግነት ያለውን አማካይ ማስፈረሙን የጋና ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።
\"\"
የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ያለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በዛሬው ዕለት ቀትር ላይ በቢሾፍቱ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን በይፋ ጀምረዋል። ከቀናቶች በፊት አማኑኤል አረቦን ከለገጣፎ ለገዳዲ ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ውጪ ሀገር በማዞር ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ክዋሜ አዶም ፍሪምፓንግን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረማቸውን የበርካታ የጋና መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አመላክቷል።
\"\"
የ26 ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው ክዋሜ በሲውዲኑ ክለብ ዳልኩርግ እንዲሁም በሀገሩ ክለቦች አሻንቲ ኮቶኮ እና በመጨረሻም አዱዋና ስታር ከተጫወተ በኋላ መዳረሻው የሀገራችን ክለብ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል።