ድሬዳዋ ከተማ አምስተኛ ተጫዋቹን አግኝቷል

ኤፍሬም አሻሞ የአሰልጣኝ አስራት አባተው ድሬዳዋ ከተማ አምስተኛው አዲሱ ፈራሚ ሆኗል።
\"\"
ዘግየት ብለው ቢሆን ወደ ዝውውሩ በመግባት ከቀናት እና ከደቂቃዎች በፊት የአራት ተጫዋቾችን ዝውውር የቋጨው ድሬዳዋ ከተማ አምስተኛ ፈራሚው ኤፍሬም አሻሞ መሆኑን ዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል።
\"\"
የቀድሞው የሐረር ቢራ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ንግድ ባንክ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዪኑቨርሲቲ እና መለቐ 70 እንደርታ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ደግሞ በድሬዳዋ የተጫወተው የመስመር አጥቂው በአንድ ዓመት ውል ከደቂቃዎች በፊት ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል።