የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ዓመቱን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የነባሮችን ውል አድሷል።

በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ መሪነት የተጠናቀቀውን የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገብቶ የስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያጠናቅቅ የነባሮችንም ውል አራዝሟል።
\"\"
እታለም አመኑ ክለቡን ተቀላቅላለች። ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘች በኋላ በሀዋሳ ከተማ ፣ ድሬዳዋ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ወደ ሀዋሳ ተመልሳ ከቆየች በኋላ ነው አማካዩዋ ወደ ኤሌክትሪክ ያመራችው። ከሀዋሳ ከተማ የክለብ ህይወትን የጀመረችው አጥቂዋ ምርቃት ፈለቀ በአዳማ እና መቻል የእግር ኳስ ህይወቷን ቀጥላ አራተኛ ክለቧ ኤሌክትሪክ ሆኗል።

ከወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ከተገኘ በኋላ በመቻል እና ሀዋሳ ግልጋሎት የነበራት አማካዩዋ ሲሳይ ገብረዋህድ የቀድሞው ክለቧን በድጋሚ ተቀላቅላለች።
አራተኛዋ ፈራሚ ዙፍን ደፈርሻ ስትሆን በአርባምንጭ ፣ አቃቂ እና ሀዋሳ በመጫወት የቆየችው አማካይዋ አዲሱ ክለቧ ኤሌክትሪክ ሆኗል።
\"\"
በአዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ የነበረችው አጥቂዋ ሳራ ነብሶ ወደ ቀድሞው ክለቧ ስትመለስ የአዲስ አበባ ከተማ የመስመር ተከላካይ ንግሥት አስረስም የኢትዮ ኤሌክትሪክ አዲስ ፈራሚ ተጫዋች ሆናለች።

በክለቡ ከአዳዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ የግብ ጠባቂዋ ማርታ በቀለ ፣ የተከላካዩቹ ዘለቃ አሰፋ ፣ ሀብታም እሸቱ እና መስከረም ካንኮ ፣ የአማካይዋ ዙለይካ ጀሀድ እና አጥቂዋ ሽታዬ ሲሳይ ውላቸውን ተራዝሞላቸዋል።\"\"