ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን የኮከቦችን ምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል

በ2015 የኢትዮጵያ እግርኳስ ውድድር ላይ የዓመቱን ኮከብ ተጫዋቾች በክለብ አምበሎች ያስመረጠው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ውጤቱን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መላኩ ታውቋል።

\"\"
የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በ 2015 የኢትዮጵያ እግርኳስ ውድድር ላይ የዓመቱን ኮከብ ተጫዋች እንዲሁም የዓመቱ ኮከብ ወጣት እና ተስፈኛ ተጫዋች በየክለቡ ላሉት የክለብ አምበሎች በላከው መጠይቅ መሠረት ተጫዋቾች የራሳቸውን ኮከቦች መምረጣቸውን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

በዚህም የ 2015 ዓ/ም ኮከብ እግርኳስ ተጫዋች የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቢኒያም በላይ ሲያሸንፍ ከወጣቶች ኮከብ እግርኳስ ተጫዋች በመሆን ደግሞ የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ መመረጥ ችሏል።
\"\"
ማኅበሩ ለተመረጡ ኮከብ ተጫዋቾች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክትም አስተላልፏል።