ታፈሰ ሰለሞን ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሷል

በፋሲል ከነማ የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው ታፈሰ ሰለሞን ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል።
\"\"
የአሰልጣኝ ዘርዐይ ሙሉን ኮንትራት በማራዘም በመቀጠል ወደ ዝውውሩ ገብተው እንየው ካሳሁን፣ አማኑኤል ጎበና እና ፂሆን መርዕድን የግላቸው ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች አራተኛ አዲሱ ፈራሚያቸው በዛሬው ዕለት የቀድሞው የክለቡ አማካይ ታፈሰ ሰለሞን መሆኑን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
\"\"
የቀድሞው የኒያላ አማካይ ከ2008 ጀምሮ ደግሞ ወደ ሀዋሳ አምርቶ ለአራት ዓመታት በክለቡ የቆየ ሲሆን በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት በፋሲል ከነማ አሳልፏል። ከፋሲል ጋር በመጨረሻዎቹ የሊጉ ሳምንታት ላይ ከአሰልጣኙ ጋር በነበረ ያለ መግባባት ክለቡን ያላገለገለው ተጫዋቹ ወደ ቀድሞው ክለቡ ሀዋሳ ተመልሶ በዛሬው ዕለት የሁለት ዓመት ውል ፈርሟል።