ቤተ ኢስራኤላዊው ተጫዋች አዲስ ክለብ አግኝቷል

ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጫወት ፍቃደኝነቱን አሳይቶ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል።

\"\"
የሀያ ሁለት ዓመቱ ቤተ ኢስራኤላዊ የአጥቂ አማካይ ዴቪድ ተሻገር ደጉ አዲሱ የውድድር ዓመት ከመጀመሩ በፊት አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል። በ2021 የውድድር ዓመት ከቤይተር ጄሩሳሌም ሁለተኛ ቡድን አድጎ ባለፈው ዓመት ከዚ ቀደም አስራት መገርሳ በተጫወተበት ሀፖይል ራማት ሀሻሮን የውሰት ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁ ተከትሎ ሌላው በኢስራኤል ሁለተኛ የሊግ እርከን ተሳታፊ የሆነውን ኢሮኒ ኪርያት ሻሞና ተቀላቅሏል።
\"\"
ተጫዋቹ ከዚ ቀደም ለእስራኤል ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የተጫወተ ሲሆን ዴቪድ በሻህ ባደረገው ጥረትም ኢትዮጵያን ወክሎ በካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ፍቃደኛ መሆኑን ገልፆ ነበር።