የፈረሰኞቹን የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ኬኒያዊያን ዳኞች ይመሩታል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ኬኤምኬኤምን ዳሬሰላም ላይ ሲያስተናግድ ኬኒያዊያን ዳኞች ጨዋታው ይመሩታል።

\"\"

የ2023 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ መደረግ ይጀምራሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን ነሀሴ 13 ዕለተ ዕርብ 10 ሰዓት ላይ ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም ጋር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በሚገኘው አዛም ኮምፕሌክስ ስቴዲየም ላይ ሲያደርግ አራት ኬኒያዊያን ዳኞች ጨዋታውን እንዲመሩ በካፍ ተመድበዋል።

በመሐል ዳኝነት ብሮኪ ፊሊፕ ሲመሩት ቶኒ ኬዲያ እና ኦሊቭ ኦሞዲ በረዳት ዳኝነት እስራኤል ማፖይማ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ጨዋታውን በጣምራ ይመሩታል። የጨዋታው ኮሚሽነር ደግሞ ከኤርትራ መሆናቸው ታውቋል።

\"\"