​በደቡብ ካስቴል ዋንጫ ሁለተኛ ቀን ጨዋታ ደቡብ ፖሊስ አሸንፏል

[በለጠ ኢርቤሎ – ከሆሳዕና]

የደቡብ ካስትል የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዋንጫ ሁለተኛ ቀን ውሎ በምድብ ለ አንድ ጨዋታ ሲደረግ ደቡብ ፓሊስ ሀምበሪቾ ዱራሜን 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

የቀድሞ የሆሳዕና ከነማ ተጫዋችና አሰልጣኝ የነበሩት ተረፈ ታደሰ እና ግርማ ታደሰን ባገናኘው የ9:00 የሀምበሪቾ ዱራሜና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ ሀምበሪቾ በኳስ ቁጥጥር ፣ ደቡብ ፖሊስ ደግሞ ወደ ግብ በመድረስ የተሻሉ ነበሩ፡፡ በ40ኛው ደቂቃ አማካዩ አበባየሁ ዮሐንስ ከመሃል ያሻገረለትን ኳስ አንጋፋው ኬኒያዊ አጥቂ ኤሪክ ሙራንዳ ተቆጣጥሮ ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ በማስቆጠር የመጀመሪያው አጋማሽ በፖሊሶች መሪነት ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ሀምበሪቾ የአቻነቷን ግብ ለማስቆጠር ጫና መፍጠር ቢችሉም ውጤቱን ለማስጠበቅ መከላከልን የመረጡተ ፖሊሶች የሀምበሪቾን የማጥቃት እንቅስቃሴ ተቆጣጥረው አሸንፈው መውጣት ችለዋል፡፡

የነገ ጨዋታዎች

06:00 ዲላ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ

08:00 ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ቤንች ማጂ ቡና

10:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ስልጤ ወራቤ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *