ኢትዮጵያ መድን ከተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

ለአንድ ዓመት ኢትዮጵያ መድንን ያገለገው ተከላካይ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

አምስት ተጫዎችን በማስፈረም ለቀጣይ የውድድር ዓመት ራሱን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ የገባው ኢትዮጵያ መድን በቅርቡ ከአማካይ ሀብታሙ ሸዋለም ጋር በስምምነት መለያየቱ ሲታወስ አሁን ደግሞ ከተከላካዩ ፀጋሰው ድማሙ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

የአንድ ዓመት የውል ዘመን እየቀረው ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው ፀጋሰው ከዚህ ቀደም ለሀዲያ ሆሳዕና፣ ሀዋሳ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወቃል።