ወደ ዩጋንዳ የሚያመራው የንግድ ባንክ ልዑክ ዝርዝር ታውቋል

የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ለማድረግ ዛሬ ከሰዓት 9 ሰዓት ወደ ዩጋንዳ የሚያመራው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልዑካን ቡድን ዝርዝር ተገልጿል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በማንሳቱ ሀገራችንን ወክሎ በቻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚያሳትፈውን የማጣሪያ ውድድር ለማድረግ ሲሰናዳ የነበረው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ወደ ስፍራው ጉዞ ይጀምራል። በዚህ ጉዞ 20 ተጫዋቾች እንዲሁም 10 የአሠልጣኝ ቡድን አባላት እና የአሰተዳደር ሰዎች በአጠቃላይ 30 የልዑካን ቡድን እንደተካተቱ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው በሀዋሳ እና በአዲስ አበባ በነበራቸው የልምምድ መርሐ-ግብር 25 ተጫዋቾችን ይዘው የነበረ ቢሆንም ለጉዞው 5 ተጫዋቾችን ቀንሰው ከስር የተጠቀሱት 20 ተጫዋቾች ወደ ስፍራው እንዲያቀኑ መወሰኑ ታውቋል።

ግብ ጠባቂዎች

ንግስት መዓዛ
ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ናርዶስ ጌትነት
ብዙዓየሁ ታደሠ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
መሰሉ አበራ
ብርቄ አማረ
ድርሻዬ መንዛ
እፀገነት ብዙነህ

አማካዮች

ንቦኝ የን
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ
መሳይ ተመስገን
ብርቱካን ገብረክርስቶስ

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ
መዲና ዐወል
አረጋሽ ካልሳ
ሴናፍ ዋቁማ
ትንቢት ሳሙኤል
አርየት ኦዶንግ

የአሠልጣኝ ቡድን አባላት

ዋና አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው
ምክትል አሠልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ
የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ንጉሴ ወ/አማኑኤል
የቡድን መሪ ተሾመ መተኪያ
ፊዚዮቴራፒስት ስንታየሁ ተሾመ
የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ቃልኪዳን ዘገየ