ድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተካፋዩ ድሬዳዋ ከተማ የአንድ ግብ ጠባቂን ዝውውር ሲያገባድድ የሁለት ነባሮችን ውልም አራዝሟል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የላቀ ተሳትፎን ለማድረግ በማሰብ ከሰሞኑ በርከት ያሉ ዝውውሮችን እየቋጨ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ማምሻው የአንድ ተጨማሪ ተጫዋችን ዝውውር ሲቋጭ የሁለቱን ውል አድሷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለፉትን አራት ዓመታት ቆይታን ማድረግ የቻለችው የግብ ዘቧ አያንቱ ቶሎሳ ድሬዳዋን ተቀላቅላለች።

ድሬዳዋ ከተማ ከአያንቱ በተጨማሪ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል። የቀድሞው የባህርዳር ተጫዋች የነበሩት የተከላካይ አማካዩዋ ቃልኪዳን ተስፋዬ እና የአጥቂዋን ሊዲያ ጌትነትን ውል ለተጨማሪ ዓመት ክለቡ አራዝሟል።