ኢትዮጵያ ቡና ዩጋንዳዊ ተከላካይ አስፈርሟል

በሰርቪያዊ አሰልጣኝ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዩጋንዳዊ የመሐል ተከላካይ አስፈርመዋል።

በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከሚያስፈርሟቸው ሁለት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል የአንደኛውን ዝውውር ቋጭተዋል። በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪች የሚመራው ክለቡም ዩጋንዳዊውን የመሐል ተከላካይ ጂኦፎሪ ዋሳዋን በሦስት ዓመት ውል የግሉ አድርጓል።

የ26 ዓመቱ ተከላካይ በሀገሩ ክለቦች ካምፓላ ሲቲ ፣ ቫይፐርስ እና በኤስ ሲ ቪላ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ነው የኢትዮጵያ ቡና አዲሱ ተጫዋች መሆን የቻለው።