ወልቂጤ ከተማ አማካይ አስፈርሟል

ዘግይተው ወደ ዝውውሩ የገቡት ወልቂጤ ከተማዎች አንድ አማካይ ማስፈረማቸው ታውቋል።

በአሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረት እየተመሩ በቅርቡ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩት ወልቂጤ ከተማዎች ከዚህ ቀደም አስር አዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ አስራ አንደኛ ፈራሚ በማድረግ አማካይ ጄላን ከማል ቡድኑን ተቀላቅሏል።

በአዳማ ተስፋ ቡድን ተገኝቶ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በጅማ አባ ጅፋር ያሳለፈው ጄላን በያዝነው ዓመት በቤንች ማጂ ቡና አንበል በመሆን ያሳለፈ ሲሆን ለቀጣይ አንድ ዓመት በሠራተኞቹ ቤት ቆይታ ለማድረግ ዝውውሩን አጠናቋል።