ቡናማዎቹ አዲስ አጥቂ ወደ ቡድናቸው ሊቀላቅሉ ነው

ኢትዮጵያ ቡና ዩጋንዳዊው አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል።


በሰርብያዊው አሰልጣኝ እየተመሩ በአዳማ ዝግጅታቸው በማድረግ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዩጋንዳዊው አጥቂ ካኮዛ ዳሬክን ለማስረፈም ተስማምተዋል። ተጫዋቹ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መግባቱ እና ነገ ወደ አዳማ በማቅናት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚጀምር ቡድኑ አስታውቋል።

የእግር ኳስ ሂወቱን በናጉሩ ፖሊስ አካዳሚ ጀምሮ በክለብ ደረጃ ለካምፓላ ፖሊስ በመጫወት ለሁለት ዓመታት ቡድኑ ያገለገለው ይህ አጥቂ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ላቲቭያ አቅንቶ ኩፕስ በተባለ ክለብ ቆይታ አድርጓል። ከላቲቭያ መልስም በግብፁ ኤንፒፒአይ ለስድስት ወራት ከተጫወተ በኋላ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

በ2021 ዩጋንዳን ወክሎ በ U21 አፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው ይህ አጥቂ ለታዳጊ ብሄራዊ ቡድን እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድን መጫወትም ችሏል።