ሽመልስ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑን መቼ ይቀላቀላል ?

የዋልያዎቹ አንበል ሽመልስ በቀለ መቼ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ታውቋል።

የፊታችን ጳጉሜ አራት ከግብፅ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን የሚከውነው ብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅቱን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ምኞት ደበበ እና ቢንያም በላይ በህመም ምክንያት ከስብስቡ ውጭ መሆናቸው ሲረጋገጥ እስካሁን ቡድኑን ያልተቀላቀለው ሽመልስ በቀለ መቼ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ሽመልስ በቀለ በሀገር ውስጥ እንደማይገኝ እና ግብፅ እንደሚገኝ የተነገረን ሲሆን በዚህም መነሻነት ብሔራዊ ቡድኑ ማክሰኞ ወደ ስፍራው የሚያቀና በመሆኑ ሽመልስ በቀለም በዛው ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።