የዋልያዎቹን እና የፈርኦኖቹን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ነገ የሚደረገውን የግብፅ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ከግብፅ አቻው ጋር ጨዋታ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በትናንትናው ዕለት ወደ ስፍራው ማቅናቱ አይዘነጋም። በካይሮ ዐየር ኃይል ስታዲየም (Air Defence) የሚደረገው ጨዋታ ከክብር እና ከደረጃ ባለፈ ምንም ውጤት ባይኖረውም ሁለቱም ቡድኖች በጥሩ ዝግጅት ጨዋታውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ይህንን ጨዋታም ጋቦናዊው ታንጉይ ፓትሪስ ምቢያም በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ሲሆን በረዳትነት ደግሞ የሀገራቸው ሰው ቦሪስ ማርሌዝ እና ኮንጎዋዊው ዳንክ ሙታሳሲ እንዲሁም ተመሳሳይ ዜግነት ያላቸው ሜሱ ንኩንኩ ግልጋሎት የሚሰጡ ይሆናል።