ሲዳማ ቡና አማካይ አስፈረመ

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በዛብህ መለዮ በይፋ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ መሪነት በሀዋሳ ዝግጅታቸው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ እየተካፈሉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በዛሬው ዕለት አማካዩ በዛብህ መለዮን በይፋ በሁለት ዓመት ውል የግላቸው ስለማድረጋቸው ዝግጅት ክፍላችን ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

እግር ኳስን በሀድያ ሆሳዕና ከጀመረ በኋላ በተለይ በወላይታ ድቻ ቆይታው ከበርካታ የስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ መታወቅ የቻለው ተጫዋቹ በመቀጠል ወደ ፋሲል ከነማ በማምራት ያለፉትን አራት ዓመታት በክለቡ ቆይታን አድርጓል። ከአፄዎቹ ጋር የሚያቆየው ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም በስምምነት መለያየት የቻለው ይህ ተጫዋች በዛሬው ዕለት በፋሲል ከነማ ካሰለጠኑት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር ዳግም የተገናኘበትን ዝውውር በሲዳማ ቡና ፈፅሟል።