ሀዲያ ሆሳዕና የአንድ ተጫዋች ዝውውር አጠናቋል

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ስብስባቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል።

ለ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን በመቅጠር ዝግጅት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሀድያ ሆሳዕናዎች በአማካይ እና ተከላካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለውን አስጨናቂ ፀጋዬን ወደ ስብሰባቸው አካተዋል።

እግርኳስን በአርባምንጭ ከተማ ሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ ጅማ አባ ጅፍር እና የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ያሳለፈው አስጨናቂ በሁለት ዓመት ውል አዲሱ የሀድያ ሆሳዕና ፈራሚ ሆኗል።