የአዲስ ግደይ ማረፊያ ታውቋል

ያለፉትን ሦስት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረው አዲስ ግደይ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከአምስት ዓመት በኋላ ዳግም የተመለሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱ ይረዳው ዘንድ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እየተሳተፈ ሲሆን የክለቡ 11ኛ ፈራሚ በማድረግ አዲስ ግደይን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

የመስመር አጥቂው በስልጤ ወራቤ ከተጫወተ በኋላ በሲዳማ ቡና ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው አዲስ ግደይ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ በማድረግ ሁለት የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወቃል። ከፈረሰኞቹ ጋር ውሉ የተጠናቀቀው ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለአንድ ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።