ከፍተኛ ሊግ | ይርጋጨፌ ቡና አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚሳተፈው ይርጋጨፌ ቡና የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥርን አጠናቋል።

የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድሩን በአሰልጣኝ ደረጀ በላይ መሪነት በምድብ ለ ዓመቱን 9ኛ ደረጃን በ35 ነጥቦች የቋጨው ይርጋጨፌ ቡና ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሱን በአዲስ አሰልጣኝ ለመቅረብ ቅጥር ፈፅሟል። በዚህም መሠረት አሰልጣኝ አላዛር መለሰ የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

በሀዋሳ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማሰልጠን ወደ ሥልጠናው ከገባ በኋላ በመቀጠል በክለብ ደረጃ በተለያዩ ጊዜያት ደቡብ ፖሊስን በረዳት አሰልጣኝነት እንዲሁም በዋና አሰልጣኝነት ያሰለጠነ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመት ደግሞ ይርጋጨፌ ቡናን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት ፊርማውን አኑሯል።