በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ የሚመሩት ሻሸመኔ ከተማዎች የመስመር አጥቂ እና ተከላካይ ላይ የሚጫወተውን ተጫዋች አስፈርመዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከረጅም ዓመታት በኋላ በማደግ የሚወዳደረው ሻሸመኔ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በቢሾፍቱ ከተማ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንደሙ መሪነት አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ ሲሰራ የሰነበተ ሲሆን ቡድኑም አለብኝ ባለው ክፍተት ላይ ያሬድ ዳዊትን በይፋ አስፈርሟል።
ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን 2008 ላይ ከተገኘ በኋላ ክለቡን ለስምንት ዓመታት በመስመር አጥቂነት እና በቀኝ መስመር ተከላካይነት ያገለገለ ሲሆን በእግር ኳስ ህይወቱ ሁለተኛ ክለቡ ሻሸመኔ መሆኑ ተረጋግጧል።