ፋሲል ከነማ የአንድ ተጫዋች ዝውውር አጠናቋል

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት ዐፄዎቹ አማካይ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ታውቋል።

ለ2016 የውድድር ዘመን ጠንካራ ዝውውሮችን በመፈፀም ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሊጉን የመጀመርያ ጨዋታቸውን ከሀዋሳ ከተማ የሚያደርጉት ፋሲሎች አማካይ አቤል እንዳለን ማስፈረማቸው ተረጋግጧል።

ምንም እንኳን ዝውውሩ በሁለቱም በኩል በተደረገ ስምምነት ቀድሞ የተጠናቀቀ ቢሆንም ከሲዳማ ቡና ጋር ያለው ቀሪ የአንድ ዓመት ውል በስምምነት ለመለያየት አንዳንድ ነገሮች እስኪጠናቀቀቁ ድርስ ሊዘገይ ቢችልም በአሁን ወቅት ከሲዳማ ቡና ጋር በስምምነት መለያየቱ ተከትሎ ዝውውሩ ሊጠናቀቅ ችሏል።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው አማካይ አቤል እንዳለ በመቀጠል በደደቢት፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በኢትዮጵያ ቡና በማስከተል በሲዳማ ቡና ሲጫወት ቆይቶ በመጨረሻ ለዐፄዎቹ ለመጫወት የሁለት ዓመት ውል አስሯል።