አዳማ ከተማ የሁለት የውጪ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

የመጀመርያ የሊጉን ጨዋታ ያለጎል ያጠናቀቀው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች በርከት ባሉ ባጧቸው ተጫዋቾች ምትክ ሰፋ ባለመልኩ ወደ ዝውውሩ መግባታቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሁለት የውጪ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ታውቋል።

የመጀመርያው ተጫዋች ተከላካዩ ሃቢብ መሐመድ ነው። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ መድን ጥሩ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታው ሁለተኛ ክለቡ በመሆን ለአዳማ ከተማ ለአንድ ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

ሌላኛው አዳማን የተቀላቀለው ናይጄሪያዊው አማካኝ ቻርልስ ሪባኑ መሆኑ ሲታወቅ ከዚህ ቀደም በሀምበሪቾ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና በባህር ዳር ከተማ መጫወቱ ሲታወቅ አሁን ደግሞ አዳማ ከተማን ለአንድ አመት ቆይታ መቀላቀሉ እርግጥ ሆኗል።