ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ አስፈርሟል

የአሰልጣኝ አስራት አባተው ድሬዳዋ ከተማ የመጨረሻውን ፈራሚ አግኝቷል።

በአሰልጣኝ አስራት አባተ የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በነገው ዕለት ሀምበሪቾ ዱራሜን አመሻሽ ላይ በማስተናገድ ወደ ውድድር ይገባል። ቡድኑ በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር እስከ አሁን ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን የመጨረሻ የቡድኑ አስረኛ አዲስ ተጫዋች በመሆን የተቀላቀለው አጥቂው ዘርዓይ ገብረሥላሴ ሆኗል።

ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ ከተማ በመጫወት በክለቡ ጥሩ የውድድር ጊዜ የነበረው አጥቂው በመቀጠል በድሬዳዋ ፓሊስ ፣ ወሎ ኮምቦልቻ ፣ ሀምበሪቾ እና አዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የቀድሞው ቡድኑ ድሬዳዋ ሆኗል።