ሲዳማ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ሲዳማ ቡና የሁለት የቀድሞው ተጫዋቾቹን ዝውውር ቋጭቷል።

ሲዳማ ቡናዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ወደ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድራቸውን ማከናወን የጀመሩት ሲሆን የዝውውር መስኮቱ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከመዘጋቱ አስቀድሞ የቀድሞው ሁለት ተጫዋቾቻቸውን ስለማስፈረማቸው ተሰምቷል።

ሀብታሙ ገዛኸኝ ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሷል። በመስመር እና በፊት አጥቂነት ለደቡብ ፖሊስ በማስከተል ከአራት ዓመታት በላይ በሲዳማ ቡና የተጫወተ ሲሆን ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ፋሲል ከነማን በመቀላቀል በክለቡ ቆይታን አድርጓል። ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ከፋሲል ጋር ዝግጅት ሲሰራ የነበረው ተጫዋቹ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት በመለያየት የቀድሞው ክለቡን ተቀላቅሏል።

ሌላኛው ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች አጥቂው ገዛኸኝ ባልጉዳ ሆኗል። በነቀምት ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና መቻል ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ ተጫዋች በነቀምት የተጠናቀቀውን ዓመት አሳልፎ ዳግም ከዚህ በፊት ወደ ተጫወተበት ሲዳማ ቡና አምርቷል።