የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አያገኙም

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ስታዲየም የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምረው የሚቀጥሉ ሲሆን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖራቸውም ተገልጿል።

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 ጅማሮውን አድርጎ በሁለተኛ ሳምንት ውድድርም ከነገ ሐሙስ ጥቅምት 1 – 2016 ጀምሮ እስከ እሁድ ጥቅምት 4 – 2016 ድረስ መካሄዱ ይቀጥላል። የሱፐር ስፖርት ቻናሎችም በዚህ ሳምንት የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ብቻ  ስለሚያስተላልፉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማያገኙ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር አሳውቋል።