የከፍተኛ ሊግ የሚጀመርበት ቀን እና የዝውውር ጊዜ ተራዝሟል

የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ዘመንን በተመለከተ በተደረገ ምክክር የጊዜ ለውጥ ተደርጓል።

በከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ሙራድ አብዲ ንግግር የተጀመረው የምክክር መድረኩ በኮሚቴው ሰብሳቢ እና በተወዳዳሪ ክለቦች የተደረገ ሲሆን በምክክሩም የውድድሩ መጀመሪያ ቀን ፣ የዕጣ የሚወጣበት ቀን እና የውድድር ቀኑ ማሻሻያ ተደርጓል።

ከዚህ ቀደም ተገልፆ የነበረው የዝውውር ቀነ ገደብ ፣ የዕጣ ማውጫ እና ውድድር መጀመርያ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም መሠረት የዝውውር ቀነ ገደቡ እስከ መስከረም 30 የነበረው ወደ ጥቅምት 19 ፣ የዕጣ ማውጫ ቀን እስከ ጥቅምት 3 ወደ ጥቅምት 10 ፣ የውድድር መጀመርያ ቀን ጥቅምት 17 የነበረው ወደ ጥቅምት 24 መሸጋገሩ ተገልጿል።