ሦስቱ ተጫዋቾች ከሀገራቸው ስብስብ ውጪ ሆነዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱት ሦስቱ ዩጋንዳዊያን በመጨረሻው የብሔራዊ ቡድን ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ ሞርሌይ ብዬክዋሶ የሚመራው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ከማሊ እና ዛምብያ ጋር ለሚያደርጋቸው ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች በጊዝያዊነት 36 ተጫዋቾች ያካተተው ስብስቡን ይፋ ማድረጉ ጠቅሰን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የሚጫወቱ ሦስት ተጫዋቾች ማካተቱ መግለፃችን ይታወሳል።

ፌደሬሽኑ ወደ ባማኮ እና ዱባይ የሚያመራው የመጨረሻ ስብስብ ይፋ ባደረገው መሰረት በመቻል የሚጫወተው ናፍያን አልዮንዚ ፣ የሀዋሳ ከተማው ቻርለስ ሉክዋጎ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ሲሞን ፒተር ከመጨረሻው ስብስብ ውጭ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ ዓርብ ከማሊ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ በኢትየጽያ አየር መንገድ ባማኮ የገባ ሲሆን ቀጣይ ማክሰኞ ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ሀሚርያ ስቴድየም ዛምብያን ይገጥማል።