ይርጋጨፌ ቡና የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥርን ጨምሮ የተጫዋቾችን ዝውውርን ፈፅሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፈው ይርጋጨፌ ቡና አዲስ አሰልጣኝ ሲቀጥር የበርካታ ተጫዋቾችን ዝውውርም አጠናቋል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ይርጋጨፌ ቡና ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ራሱን ለማጠናከር ይረዳው ዘንድ በርካታ ዓመታትን ቡድኑን ከመራው አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ ጋር በመለያየት በረዳት አሰልጣኝነት ሲያገለግል የነበረውን ዓለማየሁ ተስፋዬን በዋና አሰልጣኝነት የሾመ ሲሆን በማስከተል ወደ አስራ አራት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ አካቷል።

ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾችን ስንመለከት ፎዝያ ዝናቡ ግብ ጠባቂ ከአዳማ ፣ አማረች ኃይሉ ተከላካይ ከለገጣፎ ፣ ሜላት ንጉሴ አማካኝ ከኤሌክትሪክ ፣ ፂሆን ሳህሌ አማካይ ከአርባምንጭ ፣ አህላም ሲራጅ አማካይ ከስፖርት አካዳሚ ፣ እድላዊት ተመስገን አማካይ ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ናዝሬት ሰይፈ ተከላካይ ከፋሲል ፣ ሜሮን ገነሞ አጥቂ ከመቻል ፣ እጅጋየሁ ጥላሁን አጥቂ ከሀምበሪቾ ፣ መስከረም ምክሬ ተከላካይ ከልደታ ፣ ቅድስት በላቸው አጥቂ ከሞጆ ፣ እማቲ ደመላሽ አጥቂ ከለገጣፎ ፣ ወለላ ባልቻ ተከላካይ ከልደታ ፣ እና አዲስ ዘውገ አማካይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ መሆናቸውን ክለቡ አሳውቆናል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅት የጀመረው ክለቡም የተከላካዩዋ እየሩስ ኤልያስ እና የአማካዩዋን ትርሲት መገርሳን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።