ከፍተኛ ሊግ | ባቱ ከተማ በርከት ያሉ ዝውውሮችን አገባዷል

የ2016 የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ባቱ ከተማ የአምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የነባሮቹንም ውል አድሷል።


በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ በርከት ያሉ ዓመታትን ያስቆጠረው ባቱ ከተማ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ዝግጅት እያከናወነ ሲሆን በምድብ “ለ” ተደልድሎ ለሚያደርገው የውድድር ጊዜም ክለቡን ያጠናክራሉ ብሎ ያሰባቸውን አምስት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ ቀላቅሏል።

ክለቡን የተቀላቀሉትን ተጫዋቾች ስንመለከት የቀድሞው የሱሉልታ ፣ ሞጆ ከተማ ፣ መቂ ከተማ እንዲሁም ያለፈውን ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ከነጌሌ አርሲ ጋር ቆይታ የነበረው የተከላካይ አማካዩ ዝነኛው ጋዲሳ ፣ የአማራ ውሃ ሥራዎች የፊት መስመር አጥቂ የነበረው ወንደሰን በለጠ ፣ ያለፈውን ዓመት ከጋሞ ጨንቻ ጋር ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ አማኑኤል ተፈራ ፣ አቤኔዘር አዝቄልጬን ከይርጋጨፌ ቡና ፤ የመቂ ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ እንዲሁም ያለፈውን ዓመት ከሰበታ ከተማ ጋር ያሳለፈው ዮናስ አቡሌ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነዋል።

በተጨማሪም ክለቡ የተመስገን ሽብሩን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዝሟል።