ኢትዮጵያ ቡና ቅጣት ተላልፎበታል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ላይ የዲሲፕሊን ጥሰት ተላልፈዋል ያሉ አካላት ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በሦስተኛ ሳምንት በተደረጉ  ጨዋታዎች ዙሪያ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኞች እና የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾችን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበት የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ክለቡ ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

በተጨማሪም ለሻሸመኔ ከተማ የቡድን መሪ እና ዋና አሰልጣኙ አቶ ፀጋዬ ወንድሙ የውድድርና ሥነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግራቸው ጥሪውን አስተላልፏል።