ስታሊየኖች ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚዎች ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል።

ለ2026 የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ የተደለደሉት ቡርኪናፋሶዎች
ከጊኒ ቢሳው እና ኢትዮጵያ ላለባቸው ሁለት የማጣርያ ጨዋታዎች ስብሳቸውን ይፋ አደረጉ።
የ64 ዓመቱ አንጋፋ ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ሁበርት ቬሉድ ይፋ ባደረጉት ስብስብ የባየርን ሊቨርኩሰኑ የመሀል ተከላካይ ኤድመንድ ታፕሶባ ፣ የበርንመዙ ዳንጎ ኦታራ ፣ የሉተን ታውኑ ኢሳ ካቦሬና የአስቶንቪላው አጥቂ በርትራንድ ትራኦሬ ያካተተ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል።

በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ በ56 ደረጃነት የተቀመጡት ቡርኪናፋሶዎች ለመጨረሻ ካደረጓቸው ሰባት የአቋም መፈተሻና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በሁለቱ ስያሸንፉ ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈው በተቀሩት ሦስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።