ከዋልያዎቹ ስብስብ አራት ተጫዋቾች ተቀንሰዋል

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ አራት ተጫዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ላለበት ወሳኝ ጨዋታ 27 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ወደ ሞሮኮ የሚጓዙ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾቻቸውን ያሳወቁ ሲሆን አራት ተጫዋቾች ከስብስባቸው ውጭ መደረጋቸው ታውቋል።

እነርሱም ወልደአማኑኤል ጌቱ ፣ ብርሀኑ በቀለ፣ አለልኝ አዘነ እና ተገኑ ተሾመ መሆናቸው ሲታወቅ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ህዳር ወር መጀመርያ ላይ ከሴራሊዮን እና ቡርኪና ፋሶ ጨዋታቸውን ለማድረግ ነገ የመጨረሻ ልምምዱን በመስራት ማምሻውን በተመሳሳይ ሰዓት ለሁለት ተከፍለው ወደ ስፍራው ያቀናሉ።