ፈረሰኞቹ ሁለት ባለሙያዎችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአሰልጣኝ አባላቶች ጋር አብረው እንዲሰሩ ሁለት ባለሙያዎችን መቅጠሩ ታውቋል።

ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉት ፈረሰኞቹ የአሰልጣኝ ክፍላቸውን ለማሳደግ ሁለት የቪድዮ ተንታኝ እና ፐርፎርማንስ አናሊስት ባለሙያዎችን ስብስባቸው ውስጥ አካተዋል።

ሁለቱ ባለሙያዎች ቸርአምላክ ሀብተማርያም እና ኤፍሬም ግዛው ሲባሉ ያለፉትን ስምንት ዓመታት አር ኤንድ ዲ ግሩፕ በተንታኝነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ክለቡ በስልጠና ውስጥ ራሱን የቻለ የቪዲዮ ተንታኝ ክፍል ማዘጋጀቱትን ተከትሎ ሁለቱ ባለሙያዎች መቀጠራቸውን አውቀናል።

ከዚህ ቀደም ያላለፉት ስድስት ዓመታት ፈረሰኞቹን በቪዲዮ ተንታኝነትም ሆነ በተለያዩ የስራ መደቦች አዲስ ወረቁ ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ሱዳኑን አሊሂላል መጓዙ ይታወቃል።