ጎፈሬ የቢጫዎቹ ይፋዊ የትጥቅ አቅራቢ ሆነ

ጎፈሬ እና ወልዋሎ አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል።

በተለያዩ የሊግ እርከኖች ከተጫወቱ የትግራይ ክለቦች አንዱ የሆነውና የትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአዲስ መልክ ባዘጋጀት የትግራይ አንደኛ ዲቪዝዮን ሊግ ተሳታፊ የሆነው ወልዋሎ ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ጋር አብሮ ለመስራት ተስማምቷል። ዛሬ በዓድግራት ከተማ በተደረገው የስምምነት ስነ-ስርዓት ጎፈሬ የትጥቅ አምራች በዓመት 1.5 የሚገመቱ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ትጥቆች ለማቅረብ ከስምምነት ደርሷል።

ስምምነቱን አስመልክተው ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት የክለቡ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ዓምደመስቀል ከጎፈሬ ጋር ካደረጉት ስምምነት አስቀድመው የተለያዩ አማራጮች መመልከታቸው ጠቅሰው የምርቱ ጥራትና የተቋሙ ቀጣይ ራእይ በማየት ጎፈሬን እንደመረጡ ተናግረዋል፤ ሥራ-አስኪያጁ ጨምረውም ተቋሙ ከትጥቅ አቅርቦት ባለፈ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደርግም ገልፀዋል።