ኢትዮጵያዊው ዳኛ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል

ከጥር 4 እስከ የካቲት 3 በኮትዲቫር አዘጋጅነት የሚደረጉ የ 2023 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ለመምራት ከተመረጡ ዳኞች ውስጥ በአምላክ ተሰማ አንዱ መሆኑ ታውቋል።

ለ34ኛ ጊዜ በሚደረገው የአህጉሪቱ ትልቁ ውድድር የሆነው የአፍሪካ ዋንጫ የ 2023 የውድድር ዘመኑ ደግሞ ከጥር 4 – የካቲት 3 በኮትዲቫር በሚገኙ አምስት ስታዲየሞች እንደሚደረግ የሚጠበቅ ሲሆን 24 ሀገራትም ለፍልሚያው ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

በውድድሩ ለሚደረጉ 52 ጨዋታዎችም 26 ዋና ዳኞች ፣ 30 ረዳት ዳኞች እና 12 የቫር ዳኞች መመረጣቸው የታወቀ ሲሆን በዓለም አቀፍ መድረክ በተደጋጋሚ ጊዜ ሀገሩ ኢትዮጵያን በመወከል አድናቆት ያስተረፈው አንጋፋው ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ ውድድሩን ከሚመሩት ዳኞች መካከል አንዱ መሆኑ ታውቋል።