ኢትዮጵያ መድን የመስመር አጥቂውን ግልጋሎት ለሳምንታት አያገኝም

ያለፉትን አምስት ሳምንታት በህመም ከሜዳ የራቀው ሀቢብ ከማል ለተጨማሪ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ታውቋል።

ኢትዮጵያ መድን በወላይታ ድቻ አንድ ለምንም በተረታበት የሦስተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ወቅት ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ከወጣ በኋላ ያለፉት አምስት ሳምንታት ከሜዳ የራቀው የመስመር አጥቂው ሐቢብ ከማል ለተጨማሪ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልፆል።

የጡንቻ መሰንጠቅ ህመም ያጋጠመው ተጫዋቹ ከተወሰኑ ሳምንታት ዕረፍት በኋላ ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ ቢጠበቅም ህመሙ ከተገመተው በላይ ተጨማሪ ዕረፍት እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል። በዚህም መነሻነት ቡድኑ የአንደኛው ዙር ውድድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የሀቢብ ከማልን ግልጋሎት እንደማያገኝ እርግጥ ሆኗል።