ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተላልፏል

ከፊቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለሚጠብቀው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

በሴቶች ከ 17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በመጪው የካቲት ወር ላይ የሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። ራውዳ ዓሊን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው ቡድኑ በምክትል አሰልጣኝነት ኤርሚያስ ዱባለ እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት አብዱልከሪም ሀሰንን ማካተቱንም ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

በመጪው ሰኞ በፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት በመገኘት ሪፖርተ አድርገው ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ የተላለፈላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ሆኗል :-

ግብ ጠባቂዎች

ሮማን አምባዬ (ቦሌ ክ/ከተማ)
በረከት ዘመድኩን (ሲዳማ ቡና)
አበባየሁ ጣሰው (መቻል)
ሊንጎ ኡማን (ቦሌ ክ/ከተማ)
ፅናት አደፍርስ (ቂርቆስ)

ተከላካዮች

ለምለም አስታጥቄ (አርባምንጭ ከተማ)
ፅግነሽ ኦዳ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ማራኪ ጌቱ (ሲዳማ ቡና)
ብሌን ኃይሉ (ኢትዮ ኤሌከትሪክ)
ፍቅረአዲስ ገዛኸኝ (ቦሌ ክ/ከተማ)
አሶሬ ሀይሶ (ባህር ዳር ከተማ)
መቅደስ ታፈሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ኤልሳቤጥ ታምሩ (ሀምበርቾ)
ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ቃልኪዳን ዘላለም (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ )

አማካዮች

ሂሩት ተስፋዬ (አዲስ አበባ ከተማ)
ሚሊዮን ጋይም (ቦሌ ክ/ከተማ)
ሜሮን አበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሔለን መንግሥቱ (ሀምበርቾ)
ማንአዩሽ ተስፋዬ (ልደታ ክ/ከተማ)
ሳሮን ሰመረ (ሀምበርቾ)
ብዙአየሁ ፀጋዬ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ሀና በኃይሉ (ሀምበርቾ)
ሜላት ጌታቸው (ቦሌ ክ/ከተማ)
ቤተልሔም ሽመልስ (ፋሲል ከነማ)

አጥቂዎች

ታሪኳ ጴጥሮስ (ሀዋሳ ከተማ )
ሰርካለም ባሳ (አርባ ምንጭ ከተማ)
ቃልኪዳን ጥላሁን (ድሬዳዋ ከተማ )
ዳግማዊት ሰለሞን (አዲስ አበባ ከተማ)
ፍሬነሽ ዮሐንስ (ሀምበርቾ)
ቤዛዊት ንጉሤ (ሲዳማ ቡና)
ሳባ ኃ/ሚካኤል (አዳማ ከተማ)
ህዳአት ካሡ (ልደታ ክ/ከተማ)
ትዕግስት ወርቄ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ዓይናለም ዓለማየሁ (አዲስ አበባ ከተማ)