የአሰልጣኞች አስተያየት| ወላይታ ድቻ 2 – 1 ወልቂጤ ከተማ

“ቡድን ግንባታ ላይ ነን” – ያሬድ ገመቹ

“ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ያሳዩት ነገር ጥሩ ነበር” – ሙሉጌታ ምሕረት

ብርቱ ፉክክር ተደርጎበት በጦና ንቦች አሸናፊነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ

ስለ ጨዋታው

እጅግ በጣም ውብ ለተመልካችም የሚያዝናና ጨዋታ ነበር።

ስለ ሁለተኛው አጋማሽ እንቅስቃሴያቸው

ከዕረፍት እንደተመለስን እንደጀመርንበት ፍጥነት አልቀጠልንም፤ በዛች ቅፅበት ትኩረት በማጣታቸው ጎል ተቆጠረብን። ከዛ በኋላ ግን ተነቃቅተው ጠንክረው ተጫውተዋል። በርካታ ግቦችም ግብ ጠባቅያቸው አድኗል፤ በዚ አጋጣሚ ጎበዝ ግብ ጠባቂ ነው ማድነቅ ይገባል። ሌሎች ተጨማሪ ግብ መሆን የሚችሉ ኳሶችንም አድኖ ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ችለናል።

የአጨራረስ ችግራቹ ተቀርፋል ?

ሙሉ ለሙሉ አይተቀረፈም ይቀራል፤ ወደ ፊት እየተስተካከለ ይመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ግን አሁንም ገና ይቀረናል፤ ተጫዋቾቻችን ላይ መስራት ይጠበቅብናል።

ቀጣይ ምን እንጠብቅ

በዚ ዓመት ቡድን ነው የምንገነባው፤ ቡድን ግንባታ ላይ ነን። ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን ማራኪ እግር ኳስ የሚያሳይ ወጣቶች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው፤ ቀጣይ ዓመታት ለዋንጫ የሚፎካከር ቡድን መገንባት ነው ትልቁ እቅዳችን። ዘንድሮ ግን ወጣቶች እያበቃን ጎንለጎን ማራኪ እግር ኳስ እያሳየን ተፎካካሪ ቡድን ለመሆን ነው እቅዳችን።

ሙሉጌታ ምህረት – ወልቂጤ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ቆንጆ ጨዋታ ነበር፤ ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ያሳዩት ነገር ጥሩ ነበር፤ ግን እግር ኳስ ሆኖ ተሸንፈናል።


ስለ ሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ አጀማመራቸው

መጀመርያ ጎል ተቆጥሮብናል፤ ከዛ አጥቅተን ለመጫወት ሞክረናል ተሳክቶልንም ግብ አስቆጥረናል። በሁለተኛው አጋማሽም ኳሱን ተቆጣጥረን የተሻለ ነገር ይዘን ለመውጣት ነበር ያሰብነው። ባላሰብነው ሰዓት ተቀደምን ከዛ በኋላ ነው ቡድናችን የወረደው። ዳግመኛ ማንሰራራትን ችለን ነበር በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ ነበርን።