የወልቂጤ የቡድን አባላት ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል

የፊታችን ዓርብ ከፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታ ያለባቸው ወልቂጤ ከተማዎች ዝርፊ እንደተፈፀመባቸው ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

የፊታችን ዓርብ በአስረኛ ሳምንት ከፋሲል ከነማ ጋር የሊጉን ጨዋታ የሚያከናውኑት ወልቂጤ ከተማዎች ባረፉበት ጌት ሆቴል ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ተጫዋቾቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ዛሬ ረፋድ ላይ የቡድኑ አባላት መደበኛ ልምምዳቸውን ለመስራት ወደ ሜዳ ይወጣሉ። የዕለቱ ልምምዳቸውን አጠናቀው ሲመለሱ ግምቱ ወደ ሀያ የሚጠጋ የእጅ ስልክ ከተጫዋቾች የመኝታ ክፍል እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ የማይታወቅ የእጅ ሰዓት እና የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን እንደተሰረቁ እንዳረጋገጡ ነግረውናል።

አሁን ጉዳዩን በአካባቢው ላለው የፖሊስ መምርያ ሪፖርት ለማድረግ ተጫዋቾቹ እየሄዱ ሲሆን የሊጉ አወዳዳሪ አካልም ጉዳዩን እንደሰማ ለማወቅ ችለናል። በቀጣይ በዚህ ዙርያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።