እዮብ ዛምባታሮ አዲስ ክለብ አግኝቷል

የአታላንታ አካዳዊ ውጤት የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አዲስ ክለብ ተቀላቀለ።

ከአራት የውሰት ቆይታዎች በኋላ እናት ክለቡ አታላንታን በቋሚነት ለቆ ላለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በሴሪ ‘B’ ክለብ ሌኮ ካልችዮ ሲጫወት የቆየው ይህ የግራ መስመር ተከላካይ በሴሪ ‘C’ ምድብ ‘B’ ለሚወዳደረው ቶሬስ ፌርማውን አኑሯል።

ከዓመታት በፊት በኔራዙሪዎቹ ቤት ትልቅ ተስፋ ከሚጣልባቸው ተጫዋቾች መሀል የነበረው ይህ የሀያ አራት ዓመት ተጫዋች በ2018 ከፓዶቫ ጋር የሴሪ ‘C’ ሱፐር ኮፓ ካሳካ በኋላ በአታላንታ ዋናው ቡድን ዕድል ይሰጠዋል ተብሎ ቢገመትም የቤርጋሞው ክለብ ተጫዋቹን ከማቆየት ይልቅ ለተለያዩ ክለቦች በውሰጥ መስጠትን መርጧል። ፓዶቫ፣ ሬቫና፣ ሞኖፖሊና ሌኮ ተጫዋቹ በውሰት የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው። አሁንም ከ2022 ጀምሮ በቋሚነት ሲጫወትበት ከቆየው ሌኮ በመልቀቅ በሴሪ ‘C’ ምድብ ‘B’ በሁለተኛ ደረጃነት ወደ ተቀመጠው ቶሬስ አቅንቷል።

በእ.ኤ.አ 1998 በአዲስ አበባ የተወለደው እዮብ በዘጠኝ ዓመቱ ለዛምባታሮ ቤተሰብ በጉዲፈቻ ተሰጥቶ ወደ ጣልያን ካመራ በኃላ በኦራቶርዮ እና ፍርቶሶ ታዳጊ ቡድኖች ተጫውቶ ነው አታላንታ አካዳሚን የተቀላቀለው። በዛምባታሮ ቤተሰብ ከእዮብ በተጨማሪ በዚ ወቅት ክለብ አልባ የሆነው ግብጠባቂው አክሊሉ ዛምባታሮ ይገኛል።