የግብፁ ክለብ የአቤል ያለው ዝውውር ማጠናቀቁን ይፋ አደረገ

የግብፁ ክለብ ‘Zed’ ወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለው ማስፈረሙ ይፋ አደረገ።

ከሳምንት በፊት በበየነ መረብ አማካኝነት ስምምነት ከፈፀመ በኋላ ከጉዞ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ግብፅ ሳያመራ የቆየው ይህ ፈጣን አጥቂ ወደ ጊዛው ክለብ ማምራቱ ክለቡ በይፋዊ ገፁ ይፋ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ሀያ አንድ ነጥቦች ሰብስቦ በሁለተኛ ደረጃነት የተቀመጠው በአሰልጣኝ ማግድይ አብደል አቲ የሚመራው ይህ ክለብ ውጤታማነቱን ከፍ ለማድረግ አልሞ ሰባት ግቦች ካስቆጠረው መስጦፋ ዚኮ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊው አቤል ያለው ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል። አጥቂው ከቀናት በኋላ ከሊጉ መሪ ENPPI ጋር የሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።