ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ዌልሱ ክለብ አምርቷል

ልዑል ወርቅነህ በነፃ ዝውውር ወደ ዌልሱ ክለብ ማቅናቱ ታውቋል።


ላለፉት ስድስት ወራት በእንግሊዝ ታችኛው ዲቪዝዮን ክለብ ፎረስት ሂል ፓርክ ሲጫወት የቆየው የሀያ አንድ ዓመቱ ልዑል ወርቅነህ ኃይሌ በዌልስ ሁለተኛው የሊግ እርከን ለሚሳተፈው ባክሊይ እግርኳስ ክለብ ፊርማውን አኑሯል። በእግርኳስ ሕይወቱ ሆልምስዴል፣ ዌስትፊልድና
ዌሊንግ ለተባሉ በእንግሊዝ ታችኛው ዲቪዝዮን የሚሳተፉ ክለቦች የተጫወተው ይህ የመስመር ተጫዋች ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ የለንደኑን ክለብ ለቆ በዌልስ ሁለተኛ ዲቪዝዮን ተሳታፊ ወደ ሆነው ባክሊይ እግርኳስ ክለብ አምርቷል።


በዌሊንግ ዩናይትድ ታዳጊ ቡድን ቆይታው በአንድ የውድድር ዓመት በሀያ ጨዋታዎች 19 ግቦችን እና 11 አሲስቶችን በማስመዝገብ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ማሸነፍ ችሎ የነበረው ይህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በክለቡ የሁለት ዓመታት ቆይታው በሰላሳ ዘጠኝ ጨዋታዎች ሰላሣ ሁለት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።