ባህርዳር ከተማ አጥቂ አስፈርሟል

የውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮትን በመጠቀም የጣና ሞገዶቹ ሦስተኛውን ተጫዋች የግላቸው አድርገዋል።

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የመጀመሪያውን ዙር የሊግ ተሳትፎ ደከም ባሉ ጉዞዎች ያሳለፉት ባህርዳር ከተማዎች በቀጣዩ የሁለተኛው ዙር የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአቸውን በተጠናከረ መልኩ ለመቅረብ ይረዳቸው ዘንድ ፀጋዬ አበራን ከሲዳማ ቡና ሙጂብ ቃሲምን ከሀዋሳ ከሀዋሳ ከተማ ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ሦስተኛ ፈራሚ አድርገው ወንድወሰን በለጠን የግላቸው አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ተሳታፊ በሆነው ባቱ ከተማ በፊት እና በመስመር አጥቂነት የሚጫተወተው የቀድሞው የአውስኮድ ተጫዋች የነበረው ወንድወሰን ቀጣዩ መዳረሻው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ባህርዳር ሆኗል። ተጫዋቹ በባቱ ቆይታው በከፍተኛ ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ላይ አራት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።