ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ይመራሉ

አራት ኢትዮጵያዊያን አለም አቀፍ ዳኞች በሳምንቱ መጨረሻ ዛማሌክ ከሶአር ክለብ ጋር የሚያደርጉት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ መርሀግብርን ይመራሉ።

የ2023/24 የካፍ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎች ከያዝነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት አንስቶ መደረግ ይጀምራሉ። ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የፊታችን ዕሁድ በግብፅ ዋና ከተማ በሚገኘው ካይሮ ስታዲየም ምሽት 2፡00 በምድብ ሁለት የሚገኙት የግብፁ ዛማሌክ ከጊኒው ሶአር ክለብ ጋር የሚያከናውኑትን የመልስ ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን አለም አቀፍ ዳኞች እንዲመሩት ስለ መመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ይህንን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ ሲመራው ረዳቶቹ በመሆን ፋሲካ የኋላሸት እና ሙስጠፋ መኪ እንዲሁም አራተኛ ዳኛ ሆኖ የሚያገለግለው ደግሞ ኃይለየሱስ ባዘዘው ሆኗል። በመጀመሪያው የምድቡ ጨዋታ ዛማሌክ ከሜዳው ውጪ 4ለ0 የረታ ሲሆን ምድቡንም በበላይነት እየመራ ይገኛል።