የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መሪው ቦሌ ክ/ከተማ ነጥብ ጥሏል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ9ኛ ሳምንት በመጀመሪያ ቀን ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው የሊጉ መሪ ቦሌ ክ/ከተማ bኢትዮ ኤሌክትሪክ ሽንፈት ሲያስተናግድ አዳማ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርተዋል።

ረፋድ ሶስት ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከቦሌ ክ/ከተማ ያገናኘው ሳቢው ጨዋታ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጠናቋል።

ተመጣጣኝ በነበረው በመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በርከት ያለ ለግብ የሚሆኑ አጋጣሚዎችን ማግኘት የቻለ ቡድን ነበር።ሆኖም ግን ኳሶችን መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል። ቦሌ ክ/ከተማ በአንፃሩ በኳስ ቁጥጥር ተሽሎ የተገኙ ቢሆኑም የግብ ሙከራ በማድረግ ሰገድ ደካማ የሆኑበት የመጀመረያ አጋማሽ መርሃግብር አሳልፈዋል።

ከመልበሻ መልስ ተሽለው የተገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮ ተጋጣሚያቸውን የሊጉን መሪ ነጥብ ለማስጣል ጫና ፈጥረው ሲጫወተለ ለመመልከት ተችሏል።በረከት ያለ የግብ ሙከራ ማድረግ የቻሉት ኤሌክትሪኮች የጥረታቸው ውጤት የሆነውን ግብ በ71ኛው ደቂቃ አንጋፋዋ ሽታዬ ሲሳይ አስቆጥራ ቀዳሚ አድርጋቸዋለች።

ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ ቦሌዎች የአቻነት ግብ ፍለጋ ብዙ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። ሆኖም ግን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ውጤቱን ለማስጠበቅ ወደኋላ አፈግፍገው በመከላከል በመጫወታቸው ግብ ማስቆጠር ተስኗቸው ለሽንፈት ተዳርገዋል።

የእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአዳማ መካከል የተደረገ ሲሆን ነጥብ ተጋርተው ለመውጣት ተገደዋል።

ቀን 10 ሰዓት ላይ የጀመረው ቀዝቃዛው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። እምብዛም የግብ ሙከራ ሆነ ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ ባለስመለከተው በዚህ መርሃ ግብር ሁለቱም ቡድኖች ደካማ የሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን በመፈራራት ወደኋላ ገፍተው በመከለከል መጫወታቸው ነጥብ ለመጋራታቸው መንስኤ ሆኗል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወሳኝ የሆነው ነጥብ ለማሳካት ተሽሎ ለመገኘት ጥረት ቢያደረግም አዳማ ከተማም የዋዛ አለመሆን ነጥብ እንዲጋሩ ዳርጓቸዋል። በአንደኛው አጋማሽ ሁለተም ቁድኖች አንዳንድ ለግብ የተቃረቡ ኳሶችን ማግኘት ብችሉም  በደካማ አጨራረስ ማሳካት ሳይችሉ ሲቀሩ ለመመለከት ተችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ ያን እንቅሰቃሴ የደገሙ ሲሆን ይሄ ነው ሚባል እንቅስቃሴም ሳያደርጉ ቀርተዋል። አሰልቺ የነበረው ጨዋታም ነጥብ በመጋራት መጠናቀቅ ችሏል።