አብዲሳ ጀማል አዲስ ክለብ አግኝቷል

ከአዳማ ከተማ ጋር በውዝግብ የተሞላ ግማሽ የውድድር ዓመት ያሳለፈው አጥቂ ወደ ነጭ እና ሰማያዊ ለባሾቹ ቤት አምርቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ በኋላ ክለቦች ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በዝውውሩ የነቃ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ክለቡ እስካሁን ተክለማርያም ሻንቆ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ሀይደር ሸረፋ እና አናንያ ጌታቸውን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ አምስተኛ ተጫዋቹን ከአዳማ ከተማ አስፈርሟል።

በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራውን ኢትዮጵያ መድን የተቀላቀለው ተጫዋች አብዲሳ ጀማል ነው። የቀድሞ የነገሌ አርሲ እና ለገጣፎ ለገዳዲ ተጫዋች ከ2013 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ቤት ቆይታ ያደረገ ሲሆን ከክለቡ ጋር ያለውን ውል በማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል።