ኢትዮጵያ ቡና አማካይ አስፈርሟል

በግሩም ወቅታዊ ብቃት ላይ የሚገኙት ቡናማዎቹ አንድ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።


የውድድር ዘመኑን በአሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪች መሪነት ጀምረው ያለፉትን ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ግን በምክትል አሰልጣኛቸው ነጻነት ክብሬ ስር በመሆን በእነዚህ ጨዋታዎችም ስድስት አሸንፈው ሦስት አቻ በመውጣት ከመሪው ንግድ ባንክ በስድስት ነጥቦች ዝቅ ብለው በ29 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአጋማሹ የዝውውር መስኮት አንድ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ታውቋል።


ቡድኑን የተቀላቀለው ሰንታየሁ ወለጬ ነው። በኢትዮ ኤሌክትሪክ በተለያየ ደረጃ ላይ በሚገኙ የታዳጊ ቡድኖች ጅማሮውን አድርጎ እስከ ፕሪሚየር ሊግ ድረስ ከቡድኑ ጋር የዘለቀው አማካዩ በዘንድሮው የ2016 የውድድር ዓመት በሀዲያ ሆሳዕና የግማሽ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ ማረፊያው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።