ኢትዮጵያ ቡና ከአንድ ተጫዋች ጋር ሲለያይ ተከላካዩን በውሰት ሰጥቷል

ገዛኸኝ ደሳለኝ በውሰት ወደ ሻሸመኔ ሲያመራ አማካዩም በስምምነት ከክለቡ ተለያይቷል።

ባሳለፍነው ክረምት ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት ዓመት ውል ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ አማካዩ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ነው። የቀድሞው የመቻል ፣ ደደቢት እና መቐለ 70 እንደርታ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ለገጣፎ ተጫዋች በኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዓመት ብዙም ግልጋሎት መስጠት ሳይችል ከክለቡ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል።

በተያያዘ ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘው የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ገዛኸኝ ደሳለኝ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በውሰት ሻሸመኔ ከተማን ተቀላቅሏል።